This page is a translated version of the page Wikipedia and the translation is 44% complete.
Outdated translations are marked like this.
Note: the name "Wikipedia" is often confused with several other, similar, names; please see the glossary for an explanation of these.

ለዝርዝር መረጃ List of Wikipedias ን ይመልከቱ።

የእንግሊዝኛ ዊኪፒድያ ምልክት
የአማርኛ ዊኪፒድያ ምልክት

ሥራው የተጀመረው በእንግሊዝኛ-ቋንቋ ዊኪፒድያ በእ.ኤ.አ ጃንዋሪ 15, 2001 ላይ ነው። ወድያውም የፈረንሣይኛ ቋንቋ እናም ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌሎች ብዙ ቋንቋዎች ሥራውን ተቀላቀሉ። ዓለም አቀፋዊ አሠራሩን ለማጉላት ትልልቅ ሥራዎች እየተካሄዱ ናቸው።

እስከ ማርች 2024 ድረስ ባለው መረጃ መሠረት ፥ 325 የሆኑ ዊኪፒድያዎች 100 ጽሑፎች አላቸው ፤ ከዚያ ውስጥ 170 የሚሆኑት 10,000 ጽሑፎች እና 71 የሚሆኑት ደግሞ ከ100,000 በላይ የሆኑ ጽሑፎችን አካትተዋል።

እስከ ማርች 2024 ባለው መረጃ ፥ 339 በሚሆኑ ቋንቋዎች ዊኪፒድያ ተዘጋጅቷል ፤ እነዚህም በአጠቃላይ 62,621,011 ሚሊዮን የሚሆኑ ጽሑፎችን አካትተዋል።

Milestones

በእ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 20 ቀን 2004 ላይ ፥ ዊኪፒድያ በአጠቃላይ 1,000,000 የሚሆኑ ጽሑፎችን ከ100 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያዘ።

በእ.ኤ.አ ማርች 1 ቀን 2006 ፥ የእንግሊዝኛው ዊኪፒድያ 1,000,000 ጽሑፎችን ያዘ። በእ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 9 ቀን 2006 ፥ የእንግሊዝኛው ዊኪፒድያ 2,000,000 ጽሑፎችን ያዘ። በእ.ኤ.አ ኦገስት 17 ቀን 2009 ፥ የእንግሊዝኛው ዊኪፒድያ 3,000,000 ጽሑፎችን ያዘ። በእ.ኤ.አ ጁላይ 13 ቀን 2012 ፥ የእንግሊዝኛው ዊኪፒድያ 4,000,000 ጽሑፎችን ያዘ። በእ.ኤ.አ ኖቬምበር 1 ቀን 2015 ፥ የእንግሊዝኛው ዊኪፒድያ 5,000,000 ጽሑፎችን ያዘ።

ከእንግሊዝኛው ቋንቋ ዊኪፒድያ በመቀጠል ፥ የጀርመን (እ.ኤ.አ ዲሴምበር 27 ቀን 2009) ፣ ፈረንሣይኛ (እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2010) ፣ ሆላንድኛ (እ.ኤ.አ ዲሴምበር 17 ቀን 2011) ፣ ጣልያንኛ (እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 22 ቀን 2013) ፣ መስኮብኛ (እ.ኤ.አ ሜይ 11 ቀን 2013) ፣ እስፓንኛ (እ.ኤ.አ ሜይ 16 ቀን 2013) ፣ ስዊድንኛ (እ.ኤ.አ ጁን 15 ቀን 2013) ፣ ፖላንድኛ (እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 24 ቀን 2013) ፣ ዊናራይኛ (እ.ኤ.አ ጁን 8 ቀን 2014) ፣ ቪዬትናምኛ (እ.ኤ.አ ጁን 15 ቀን 2014) ፣ ሴቡዋኖኛ (እ.ኤ.አ ጁላይ 16 ቀን 2014) እና የጃፓን እትም (እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 19 ቀን 2016) ከ1,000,000 በላይ የሆኑ ጽሑፎች ኖሯቸው።

በእ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 5 ቀን 2015 ፥ የስዊድንኛው ዊኪፒድያ እና በመቀጠልም የሴቡዋኖኛ ዊኪፒድያ በእ.ኤ.አ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2016 ፥ 2,000,000 ጽሑፎችን አካተቱ።

On 27 April 2016, the Swedish Wikipedia hit 3,000,000 articles followed by the Cebuano Wikipedia on 25 September 2016.[1]

On 11 February 2017, the Cebuano Wikipedia hit 4,000,000 articles.[1]

On 8 August 2017, the Cebuano Wikipedia hit 5,000,000 articles.[1]

On 14 October 2021, the Cebuano Wikipedia hit 6,000,000 articles.[1]

በእ.ኤ.አ 2004 ዊኪፒድያ ለ"ማህበረሰብ" የዌቢ ሽልማትን እና በ"ዲጂታል ማህበረሰብ" ደግሞ የፕሪ አርስ ኤሌክትሮኒካ ሽልማትን አሸንፏል። በእ.ኤ.አ 2015 ፥ የኢራዝመስ ሽልማት ለዊኪፒድያ ማህበረሰብ በጋራ ተሰጥቶ ነበር።

የቋንቋ እትሞች

ጽሑፎች ስለ ዊኪፒድያ

ይህንንም ይመልከቱ

Notes

  1. a b c d Some projects with a small and weak community can reach a large size due to the mass generation of low-quality content by the bot. The most striking examples of this kind are the Swedish and Cebuano Wikipedias. See also Proposals for closing Cebuano Wikipedia in October 2017.