ሞንቴካቲኒ ቴርሜ

ሞንቴካቲኒ ቴርሜ (ለ ISTAT ሞንቴካቲኒ-ቴርሜ በዳሽ የተፃፈ ሲሆን) 20,663 ነዋሪዎችን ያካተተ ፣ በቶስካኒ ክልል ፣ በፒስቶያ ጠቅላይ ግዛት የሚገኘ የጣሊያን ቀበሌ ነው። የሞንቴካቲኒ ቴርሜ ከተማ በቫልዲኒዬቮሌ ሸለቆ መሃል የሚገኘ ሲሆን ፣ ታላቅ የፍሎሃ ስፍራዋ ቱሪዝምን ዋና የአካባቢው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲሆን ያደርገዋል።

የሞንቴካቲኒ መኖር ከነፍሎሃ መአከሉ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው፣ ቀድሞውኑ ሮማዊው ታሪክ ጸሐፊ ቲቶ ሊቭዮ ሃኒባል ጣሊያንን በተሻገረበት ጊዜ ስፍራውን እንደ ረግረጋማ ገልጾት ነበር።

በ 1315 በስፍራው ላይ የሞንቴካቲኒ ጦርነት ተካሄደ፣ ጦርነቱም በኡጉቾኔ ዴላ ፋጆላ (በዛን ዘመን የፒዛና የሉካ ጌታ) እና በኔፕልስ አንጆኢኒዎች የተደገፉት ፍሎረንስ ፣ ሲዬና ፣ ፕራቶ ፣ ፒስቶያ ፣ አሬዞ ፣ ቮልቴራ ፣ ሳንጂሚንያኖ ፣ ሳንሚንያቶ ወዘተ ከተሞች የኃይል ቅንጅት።

በ 1328 የሜዲቺ ቤተሰብ ስልጣን ያዘ። የሞንቴካኒ ስፍራ ላይ ብዙ ጊዜ ጦርነት ይካሄድ ነበር፣ እንዲያውም በ 1554 የካርሎ V (የኮዚሞ l ዴ ሜዲቺ ተባባሪ) እና የሲዬናና ፈረንሳይ ሚሉሽያዎች ግጭት በፒየትሮ ስትሮዚ ትዕዛዝ ስር ተካሂዶበታል። በ 1737 የሜዲቺ ቤተሰብ ተሟጠጠ።

በ 1738 በቪየና የተሰበሰቡት ታላላቅ የአውሮፓ ኃያላን መንግሥታት ተስካኒ ለአዝቡርጎ ሎሬና እንድትመደብ ወሰኑ። በተስካኒ ግራንድ ዱክ ሌኦፖልድ II ስር በማሬማ አሮንቃ የሬክላሜሽን ስራዎች ፣ እንዲሁም የባቡር ሀዲዶች እና መንገዶች ተገንብተዋል። የሎሬና ክፍለ ጊዜ የሚጠናቀቀው በ ሪሶርጂሜንቶ ጅምር ነው።

በ 1859 ታላቁ መሰፍንት (ግራንዱካቶ) ተጠናቀቀ። በ 1898 ወደ ቤተ መንግስት የሚወስድ አሳንሰር ተመረቀ። ከ 1904 እስከ 1915 የቶሬታ እና ኤክሴሊሶር የፍሎሃ ሆቴሎች ተመሰረቱ። ጆቫኖዚ ከ 1919 እስከ 1928 የሌኦፖልዲኔንና የቴቱቾን ፍሎሃ ስፍራዎችን እድሳት ስራዎችን አካሄደ።

ሙሶሊኒም መንግስት ለፍሎሃዎቹ ጥገና የተመደበውን ገንዘብ አጠቃቀም ለመቆጣጠር ጉብኝት ሄዶ ነበር። አርቱሮ ሽቫይገርንም እንደ ፍሎሃዎቹ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ይሾማል። ከ 1970ዎቹ ዓመታት ጀምሮ ፍሎሃዎቹ ቀስ በቀስ እየተበላሹ ሲሄዱ ከ 20ኛው መቶ ዘመን ማለቂያ ላይ ኢሄን በተመለከተ ጥረቶች ጀመሩ።

በከተማው ውስጥ ከሚገኙት በጣም አስፈላጊ የፍሎሃ ግንባታዎች መካከል ኤክሴሊሶር ይገኛል ፣ የዚህ የመጀመሪያው ህንጻ በ ፈረንጅ ኣቆጣጠር ጁን 27 ቀን 1907 ላይ ተመረቀ ፣ በ 1853 የተገኘው የ ላ ፎርቱና ፍሎሃ ምንጩ ፣ በ1964 ዳገም የተገነባው የ1920 ንዎቬ ሬዲ ፍሎሃ ፣ በ1779 እና 1781 አመታት መሃል በኒኮሎ ማሪያ ጋስፓሮ ፓኦሌቲ ፕሮጀክት ኣማካይነት የተገነባው የቴቱቾ ፍሎሃ ፣ በ1775 ላይ የተጀመረው የ ሌኦፖልዲኔ ፍሎሃ እና በ1925 እና 1928 አመታት መሃል የታደሰው የቶሬታ ፍሎሃ ።

በተጨማሪም ከተማዋ በሃይማኖትና በሲቪል ሕንፃዎች የበለጸገች ናት ፣ በነዚህ መካከል የሳንታ ማሪያ አሱንታ ፣ የሳንቲ ያኮፖ እና ፊሊፖ ቤተክርስቲያኖች ፣ የሳንታ ማሪያ አ ሪፓ ገዳምና ቤተክርስቲያን ፣ ፎሪኒ ሊፒ ቪላ የማዘጋጃ ቤት ህንጻ እና ፓዲሊኦንቺኖ ታሜሪቺ ።